ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰውዬ እየሄደ ሳለ መንገድ ላይ እሾካማ ቅርንጫፍ አገኘና አራቀው። አላህም ስራውን ተቀበለው። ወንጀሉንም ማረው።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና‐ አንድ ሰውዬ መንገድ ላይ ሙስሊሞችን በሚያውክ በእሾካማ ዛፍ ቅርንጫፍ በኩል ሲያልፍ ቅርንጫፉን ከመንገዱ እንዳራቀውና አላህም ስራውን ተቀብሎ ወንጀሉን እንደማረው ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የሚያውክን ነገር ከመንገድ ላይ የማራቅን ደረጃና ይህም አንዱ የአላህን ምህረት ማግኛ ምክንያት መሆኑን እንረዳለን።
  • መልካም ስራዎች ትንሽ እንኳ ቢሆኑ ማሳነስ እንደማይገባ እንረዳለን።
  • እስልምና የንፅህና፣ የማህበረሰብን ደህንነትና የህዝብን ሰላም የሚጠብቅ ሃይማኖት ነው።