ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤቶችን እንደ መቃብር ከሶላት የተገለሉ እና ሶላት የማይሰገድባቸው ከማድረግ እየከለከሉ ነው። እንዲሁም ልማድ አድርጎ በመያዝ የሳቸውን ቀብር ደጋግሞ መጎብኘቱንም እዚያው መሰብሰቡም ወደ ሽርክ ስለሚያደርስ ከለከሉ። ከዛ ይልቅ ወደ ቀብራቸው መመላለስ ሳያስፈልግ ቅርብም ይሁን ሩቅ እኩል ለእርሳቸው ስለሚደርሳቸው ከየትኛውም ቦታ ሆነን በሳቸው ላይ ሶለዋት እንድናወርድ አዘዙን።