explain-icon

ትንታኔ

በንግግርም ይሁን በተግባር ለሌሎች የምንውለው በጎነትና ጥቅም ሁሉ ምፅዋት እንደሚሆንና በሱም ምንዳና አጅር እንደምናገኝበት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ምፅዋት የሰው ልጅ ከገንዘቡ በሚያወጣው ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን የሰው ልጅ ወደ ሌሎች በሚደርስ መልኩ የሚሰራውና የሚናገረውን ሁሉ መልካም ነገሮችን ያቀፈ ነው።
  • በዚህ ሀዲስ ውስጥ ለመልካምና ለሌሎች ጥቅም ላለው ነገር ሁሉ መልፋትን ያነሳሳል።
  • ትንሽም እንኳን ብትሆን ከመልካም ነገር አንዳችም ማሳነስ እንደማይገባ እንረዳለን።