ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመመፅወት አቅጣጫዎችን ገለፁ። የሚመፀወትባቸው አቅጣጫዎች የተደራረቡ ጊዜም በእርሶ ላይ ግዴታ ከሚሆነው አንፃር ቅደም ተከተሉ ገለፁ። እጅግ አንገብጋቢና ወሳኝ በሆነውም ጀመሩ። እጅግ በጣም ብዙ ምንዳ የሚያስገኘው ገንዘብ አንድ ሙስሊም ወጪ ግዴታ ለሆነባቸው የሚመፀውተው ገንዘብ እንደሆነ ገለፁ። ለምሳሌ ሚስት፣ ልጅና የመሳሰሉት ቀጥሎ በአላህ መንገድ ለሚደረግ ጦርነት ለተዘጋጀ መጓጓዣ የሚወጣ ወጪ ነው። ቀጥሎም በአላህ መንገድ የሚታገሉ ለሆኑ ጓደኞቹና ባልደረቦቹ መመፅወት ነው።