ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሥራዎች ስድስት ዓይነት መሆናቸውን ሰዎች ደግሞ አራት አይነት መሆናቸውን ተናገሩ። ስድስቱ የሥራ አይነቶች: - የመጀመሪያው: በአላህ ላይ አንዳችን ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ለሱ ፀናችለት። ሁለተኛ: በአላህ ላይ አንዳችን አካል እያጋራ የሞተ ሰው እሳት በሱ ላይ የፀናችና በውስጧም ዘውታሪ ነው። እነዚህ ሁለት ሥራዎች እሳትና ጀነትን የሚያፀኑ ናቸው። ሦስተኛ: የተነየተ መልካም ስራ ነው። ቀልቡ እንደሚሠራው እስኪሰማውና አላህም የኒያውን እውነተኝነት እስኪያውቅለት ድረስ በእውነተኛ ኒያ መልካም ሥራን ለመሥራት የነየተ ከዚያም ይህን የነየተውን መልካም ሥራ መሥራት እንዳይችል የሚያደርግ ጉዳይ የተጋረጠበት ሰው ሙሉ መልካም ሥራ ይጻፍለታል። አራተኛ: የተሠራች መጥፎ ተግባር ናት። መጥፎን ሥራ የሠራ ሰው አንድ መጥፎ ሥራ እንደሠራ ይጻፍበታል። ሁለቱ (ሦስተኛውና አራተኛው) ያለምንም ብዜት በሠራው ሥራ አምሳያ የሚያስመነዱ ሥራዎች ናቸው። አምስተኛ: አምሳያዋ በአስር ተባዝቶ የሚያስመነዳ መልካም ሥራ ነው። እሱም አንድን መልካም ስራ ለመሥራት ነይቶ የሠራ ሰው ለሱ አስር ምንዳ ይጻፍለታል። ስድስተኛ: በሰባት መቶ እጥፍ ተባዝቶ የሚመነዳ መልካም ሥራ ነው። እሱም አንድን ምፅዋት በአላህ መንገድ የመፀወተ ሰው ይህቺ መልካም ሥራ በሰባት መቶ ተባዝታ ትጻፍለታለች። ይህም ከፍ ያለውና የጠራው አላህ በባሮቹ ላይ የዋለው ችሮታና ቸርነት ነው። አራቱ የሰው አይነቶች ደግሞ፦ የመጀመሪያው: በዱንያ ውስጥ ሲሳዩ የሰፋለት፣ በውስጧ የሚደሰትና የፈለገውን የሚያገኝ ሲሆን ነገር ግን አኺራ በሱ ላይ የጠበበችና መመለሻው እሳት የሆነ ሀብታም ከሀዲ ነው። ሁለተኛው: በዱንያ ውስጥ ሲሳዩ የጠበበችበት ሲሆን ነገር ግን አኺራ ለሱ የሰፋችለትና መመለሻው ወደ ጀነት የሆነ ድኻ አማኝ ነው። ሶስተኛው: ዱንያም ሆነ አኺራ በሱ ላይ የጠበቡበት ድኻ ካፊር ነው። አራተኛው: ዱንያም ሆነ አኺራ ለሱ የሰፉለት ሀብታም አማኝ ነው።