ሙዓዝ ቢን ጀበል -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መጋጓዣ ኋላ ተፈናጦ ሳለ እሳቸው "ሙዓዝ ሆይ!" በማለት ጠሩት። ለርሱ የሚነግሩት ነገር አንገብጋቢ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠትም ጥሪያቸውን ሶስት ጊዜ ደጋገሙት። ሙዓዝም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- በነዚህ ጥሪዎች ሁሉ "ለበይከ ያረሱለሏህ ወሰዕደይክ" ማለትም የአላህ መልክተኛ ሆይ!ደጋግሜ በደስታ አቤት ብያለሁ። እያለ ይመልስ ነበር። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ሳይዋሽ በእውነተኛ ልቡ የሚመሰክር ሆኖ በዚህ ሁኔታው ላይ ከሞተ አላህ እሳትን በርሱ ላይ እርም እንደሚያደርግ ነገሩት። ሙዓዝም -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ሰዎች እንዲደሰቱና በመልካም እንዲበሰሩ ልንገራቸውን? በማለት ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠየቀ። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህች ንግግር ላይ በመደገፍ ስራዎቻቸው እንዳታንስ ፈሩ። ሙዓዝም እውቀትን የመሸሸግ ወንጀል ውስጥ መውደቅን በመፍራት ከመሞታቸው በፊት ካልሆነ በቀር ከዛ በፊት ይህችን ሐዲሥ ለአንድም ሰው አልተናገረም።