ጃቢር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ አንድ ሰውዬ በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሁለቱ (ጀነትና እሳት ውስጥ መግባትን) የሚያስወስኑ ነገሮች ምንድናቸው?" እሳቸውም "በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ። ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

አንድ ሰውዬ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጀነት መግባትን ስለሚያስወስን እና እሳት መግባትን ስለሚያወስን ሁለት ነገሮች ጠየቃቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና፦ ጀነትን የሚያስወስነው ነገር ሰውዬው አላህን በብቸኝነት እያመለከ በሱ አንዳችንም ሳያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት። እሳትን የሚያስወስነው ነገር ደግሞ ሰውዬው ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ አምሳያ እና አቻ በማድረግ በአላህ ላይ አንዳችን ነገር እያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የተውሒድ ትሩፋት መገለፁ። እሱም አማኝ ሆኖ በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት የሚገባ መሆኑ ነው።
  • የሺርክ አደገኝነትም መገለፁ። እሱም፥ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት የሚገባ መሆኑ ነው።
  • ወንጀልን የሰሩ የተውሒድ ሰዎች በአላህ ፍላጎት ስር ናቸው። በመሆኑም ከፈለገ ይቀጣቸውል ከፈለገም ይምራቸዋል። ከዚያም ግን መመለሻቸው ወደ ጀነት ነው።