ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አጎታቸው አቡ ጣሊብ ጣእረ ሞት ላይ ሳሉ ላኢላሀ ኢለላህን እንዲናገር ፈለጉ። ይህም የትንሳኤ ቀን በሷ ምክንያት ሊያማልዱትና በእስልምናው ሊመሰክሩለት ብለው ነው። አቡ ጧሊብ ግን ቁረይሾች እንዳይሰድቧቸው ፈርተውና "እርሱ የሰለመው ሞትና ደካማነትን በመፍራቱ ምክንያት ነው!" እንዳይባሉ በመስጋት የምስክርነት ቃሏን መናገር እምቢ አሉ። ለነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ይህ ስጋቴ ባልነበር የምስክር ቃሏን በመናገር በልብዎ ውስጥ ደስታን አስገባም ነበር እስኪደሰቱ ድረስም ምኞቶን አሳካ ነበር" አሏቸው። አላህም የፈለገውን ሰው እርሱ ብቻ እንጂ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኢስላምን በሰው ቀልብ ውስጥ በማስረፅ መምራት እንደማይችሉ የሚጠቁም አንቀፅ አወረደ። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፍጡራንን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በመጠቆም ፣ በማብራራት፣ በማቅናትና በመጣራት ነው የሚመሩት።