አጋርያን ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ብቸኛና አጋር እንደሌለው እስኪመሰክሩ፤ በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልክተኝነት እስኪመሰክሩና ይህ የምስክር ቃል በሚያስፈርደው ነገሮች እስከሚተገብሩ ለምሳሌ በቀንና ምሽት ውስጥ አምስት ሶላቶችን መስገድ ላይ በመጠባበቅ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ ለሚገባው እስኪሰጡ ድረስ አላህ አጋርያንን እንዲጋደሉ እንዳዘዛቸው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ። እነዚህን ጉዳዮች የሰሩ ጊዜ ኢስላም ደማቸውንና ገንዘባቸውን ይጠብቅላቸዋል። በኢስላም ህግጋት መሰረት ለግድያ የሚያበቃቸውን ወንጀል ወይም ጉዳት እስካልፈፀሙ ድረስም እነርሱን መግደል አይፈቀድም። ከዚያም እነርሱን መተሳሰቡን የትንሳኤ ቀን ውስጣቸውን በሚያውቀው አላህ ቁጥጥር ይሆናል።