ከሙሽሪኮች የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። አብዝተው የገደሉና የዘሞቱ ነበሩ። ለነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: የምትጣራው ኢስላምና አስተምህሮቶቹ መልካም ጉዳይ ነው። ነገር ግን የወደቅንበት ሺርክና ከባድ ወንጀል ለርሱ ማስማሪያ አለውን? ወንጀላቸው ከመብዛቱና ከመተለቁ ጋርም አላህ ከሰዎቹ ተውበታቸውን እንደተቀበለ የሚጠቁሙ ሁለት አንቀፆች ወረዱ። ይህ ባልነበር ኖሮ በክህደታቸውና ጥመታቸው ላይ ይቀጥሉ ነበር። ወደዚህ ሃይማኖትም አይገቡም ነበር።