ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙዐዝ ቢን ጀበልን - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ወደ አላህ መንገድ ተጣሪና አስተማሪ በማድረግ ወደ የመን በላኩበት ወቅት ከክርስቲያን የሆኑ ህዝቦችን ስለሚጋፈጥ እነርሱን በተመለከተ ዝግጁ እንዲሆን አሳሰቡት። ቀጥለውም ዳዕዋውን እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ነጥብ እንዲጀምር ነገሩት። መጀመርያ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" ብለው በአሏህ አንድነትና በሙሐመድ መልዕክተኝነት በመመስከር እምነታቸውን እንዲያስተካክሉ ጥሪ እንዲያደርግ፤ ምክንያቱም ወደ እስልምና የሚገቡት በዚህ የምስክርነት ቃል ስለሆነ ነው። ይህንንም ተግባራዊ ካደረጉ ሶላትን እንዲሰግዱ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ምክንያቱም ከተውሒድ በኋላ ትልቁ ግዴታ ሶላት ስለሆነ ነው። ሶላትንም ካስተካከሉ በኋላ ከመካከላቸው ያሉት ባለ ፀጎች በመካከላቸው ላሉት ድሆች ከገንዘባቸው ዘካን እንዲያወጡ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለዘካ ብሎ ከውድ ንብረታቸው እንዳይወስድ አስጠነቀቁት። ምክንያቱም የመስጠት ግዴታቸው ከመካከለኛ ንብረታቸው ነውና። ከዚያም የተበዳይ ዱዓእ ተቀባይነቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተበዳይ ዱዓእ እንዳያደርግበት ግፍን መጠንቀቅ እንዳለበት አሳሰቡት።