ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በአማኞች ላይ የዋለውን ትልቅ ችሮታና ከከሀዲያን ጋር ያለውን ፍትሀዊነት ያብራራሉ። አማኝ የሆነ ሰው የመልካም ሥራው ምንዳ ምንም አትጎድልም። በአኺራ ከሚደለብለት (ከሚከማችለት) ምንዳ በተጨማሪ በዱንያም በአምልኮው ምክንያት መልካምን ይሰጠዋል። ይህ ካልሆነ እንኳ ሁሉም ምንዳው ለሱ አኺራ ላይ ይጠበቅለታል። ካፊር ግን ለሠራው መልካም ሥራ የሚመነዳው በዱንያ አላህ በሚሰጠው መልካም ነገር ነው። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ ምንም የሚመነዳው ክፍያ አይኖረውም። ምክንያቱም በመልካም ሥራ በሁለቱም ዓለም ለመጠቀም የግድ ባለቤቱ አማኝ መሆን ይጠበቅበታል።