ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን ከሒሳብ መተሳሰቢያ ስፍራ አንድም ሰው ስለተወሰኑ ጉዳዮች ሳይጠየቅ ወደ ጀነት ወይም ወደ እሳት እንደማያልፍ ተናገሩ። የመጀመሪያው: ህይወቱን በምን እንዳጠፋውና እንዳሳለፈው? ሁለተኛው: ዕውቀቱን ለአላህ ብሎ ነው የፈለገው? በእውቀቱ ሰርቶበታልን? ማወቅ ለሚገባውስ አስተላልፎታልን? ሶስተኛው: ገንዘቡን ከየት ነው ያገኘው? ከሐላል ነው ወይስ ከሐራም? ለምንስ አዋለው? አላህን በሚያስደስት ነገር ላይ አዋለው? ወይስ በሚያስቆጣው ነገር ላይ? አራተኛው: ስለ አካሉ፣ ሀይሉ፣ ጤንነቱ፣ ወጣትነቱ ነው። ምን ላይ ተጠቅሞ እንዳሳለፈው?