ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሙስሊም ወንድሙን በክብሩ ወይም በገንዘቡ ወይም በደሙ የበደለ ሰው ነፍሱን ለማዳን ለበደለው ሰው የሚሰጠው የወርቅ ዲናርም ሆነ የብር ዲርሃም የማይጠቅምበት የትንሳኤ ቀን ከመምጣቱ በፊት በዱንያ ውስጥ እስካለ ድረስ የተበዳዩን ይቅርታ እንዲጠይቅ አዘዙ። የትንሳኤ ቀን ፍርድ የሚሰጠው በመልካም ስራዎችና ሀጢአቶች ነውና። ተበዳዩ ከበዳዩ መልካም ስራዎች ቀንሶ የተበደለውን ያህል መልካም ስራዎችን ይወስዳል። በዳዩ መልካም ስራዎች ከሌሉት በበደሉ ልክ ከተበዳዩ ወንጀሎች ተወስደው በበዳዩ ላይ ይደረጋሉ።