ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የትንሳኤ ቀን የሚከሰተውን አንድ ክስተት እንዲህ በማለት ገለፁ። ሰዎች ለሒሳብ ከቀብራቸው ከተቀሰቀሱ በኋላ ያለ ጫማ በባዶ እግራቸው፣ ያለልብስ ሰውነታቸው ተራቁቶና እናታቸው እንደወለደቻቸው ቀን ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ። ይህንንም የአማኞች እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ስትሰማ ተደንቃ እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወንዶችም ሴቶችም ባጠቃላይ ከፊሉ ወደ ከፊሉ እየተመለከተ?" ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከሞት መቀስቀስ በኋላ የመሰብሰብና የመቆም ጉዳይ ሀፍረተ ገላን ከመመልከትም በላይ የሰዎችን ሃሳብና አይን የሚሰልብ አስደንጋጭነት እንዳለው ገለፁ።