ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመጪው አለም ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች እንዳሉ፤ በየሁሉም ደረጃዎች መካከል የሚገኘው ርቀት በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ያህል ርቀት እንደሆነ፤ ከነዚህ ጀነቶች መካከል ከፍተኛዋ ጀነት ፊርደውስ እንደሆነች፤ አራቱ የጀነት ወንዞች የሚመነጩትም ከርሷ መሆኑን፤ ከፊርደውስ በላይም ዐርሽ መሆኑንና ፊርደውስም ከሁሉም ጀነቶች በላይ ስለሆነች አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት ብለው ተናገሩ።