አንድ ከአለቃው ጋር ነፍሱን ለመግዛትና ነፃ ሊያወጣት ተስማምቶ የተፃፃፈ ነገር ግን ገንዘብ የሌለው ባሪያ ወደ አማኞች አዛዥ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - መጣና እንዲህ አለ: "እኔ ያለብኝን ገንዘብ መክፈል አቅቶኛልና ገንዘቡን በመክፈል ላይ ወይም መፍትሄ የሚሆነኝን በማስተማርና በመጠቆም ላይ አግዘኝ።" የአማኞች አዛዥም እንዲህ አለው: "ጦይእ አካባቢ ውስጥ የሚገኘው የሲር ተራራን የሚያህል እዳ ቢኖርብህ እንኳ አላህ እዳህን ለሚገባው አካል በመክፈል ከመዋረድ እንድትድን የሚያደርግን የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ያስተማሩኝን ቃላቶች ላስተምርህን?" ቀጥሎ እንዲህ አለው: "እንዲህ በል (አልላሁመ ክፊኒ) አላህ ሆይ አርቀኝ፣ አዙረኝ (ቢሐላሊከ) በሐላልህ ተብቃቅቼ (ዐንሐራሚክ) ክልክልህ ላይ ከመውደቅ (ወአግኒኒ) አብቃቃኝ (ቢፈድሊከ) በቸርነትህ (ዐመንሲዋክ) ከአንተ ውጪ ካሉ ፍጡራን።