ከቁጥባህ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ ከመጥፎ ስነ ምግባራት፣ ከመጥፎ ስራዎችና ከመጥፎ ዝንባሌዎች በአንተ እጠበቃላሁ።"» ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ከነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ዱዓዎች መካከል: (አልላሁመ ኢኒ አዑዙ) አላህ ሆይ! እኔ ወደ አንተ እጠጋለሁ፣ ጥበቃህን እፈልጋለሁ። (ቢከ) ሌላውን ትቼ በአንተ ብቻ (ሚን ሙንከራቲ) አላህና መልክተኛው ከከለከሉት ፀያፍ (አልአኽላቅ) እንደ ምቀኝነት፣ ጥላቻና ኩራት ካሉ ስነ ምግባራት (ወልአዕማል) እንደመሳደብና መዝለፍ ካሉ ፀያፍ ተግባራት (ወልአህዋእ) ሸሪዓን ከሚፃረሩ ነፍስ የሚመኛቸው ከሆኑ ዝንባሌዎች (ባንተ እጠበቃለሁ) ማለት ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የዚህን ዱዓ ደረጃና ተወዳጅነት እንረዳለን።
  • አማኝ የሆነ ሰው ውግዝ ስነምግባራትንና መጥፎ ተግባራትን ለመራቅ ይጥራል። ዝንባሌውን ከመከተልና ስሜት ላይ ከመውደቅም ይጠነቀቃል።
  • ስነምግባር፣ ስራዎችና ዝንባሌዎች ወደ መጥፎና ጥሩ ለሁለት እንደሚከፈሉ እንረዳለን።
explain-icon

ተጨማሪ