ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓኢሻን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ጠቅላይ ዱዓዎችን አስተማሯት። እነርሱም እነዚህ አራት ዱዓዎች ናቸው: የመጀመሪያው: ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ዱዓ ነው (አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ሁሉንም እጠይቅሃለሁ) አጠቃላዩን (ቅርቡንም) ወቅቱ የቀረበውን (የዘገየውንም) መምጫ ወቅቱ የራቀውንም (ከርሱ ያወቅኩትንም) ካሳወቅከኝም (ያላወቅኩትንም) ከአንተ እውቀት ብቻ ከሆነውም እጠይቅሃለሁ። በዚህም ነገሮችን አዋቂና ውስጠ አዋቂ ወደሆነው አላህ ብቻ ማስጠጋት አለበት። ይህንን ዱዓ ላደረገ ሙስሊም አሏህ በላጩንና የተሻለውን ይመርጥለታል። (ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም ነገር) (መጠበቂያዬ) መጠጊያዬ አንተው ነህ። ሁለተኛው ዱዓ: አንድ ሙስሊም በዱዓው ወሰን ከማለፍ ጥበቃን የሚጠይቅበት ነው። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጠየቁህን መልካም ነገር) (አላህ ሆይ እኔ እጠይቅሃለሁ) ከአንተ እፈልጋለሁ። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም) (ባንተ እጠበቃለሁ) እጠጋለሁ። በዚህ ዱዓ ጠያቂው ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የለመኑትን የዱዓ አይነቶች ሳይቆጥር እርሳቸው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህን ከለመኑትና ከርሱ ከፈለጉት የተሻለውን እንዲሰጠው እየጠየቀ ነው። ሶስተኛው ዱዓ: ጀነት መግባትና ከእሳት መራቅን መፈለግ ነው። ይህም የሁሉም ሙስሊም ፍላጎትና የስራው ግብ ነው። (አላህ ሆይ! ጀነትን) በርሷ መጎናፀፍን (ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባርን እጠይቅሃለሁ።) የሚያስደስትህን መልካም ስራ እጠይቅሃለሁ። (ከእሳትም በአንተ እጠበቃለሁ።) በአንተ እዝነት ካልሆነ በቀር ከፀያፍ ተግባር መጠበቂያ የለምና። (ወደርሷ ከሚያቃርብ ንግግር ወይም ተግባርም በአንተ እጠበቃለሁ።) ከሚያስቆጣህ ወንጀል በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው። አራተኛው ዱዓ: በአላህ ውሳኔ የመውደድ ዱዓ ነው። (ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝ እጠይቅሃለሁ።) አላህ ለኔ የወሰነውን ነገር ሁሉ ለኔ መልካም እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ። ይህም በአላህ ፍርድ የመውደድ ዱዓ ነው።