አብዛኛው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓ በኢስላምና በአምልኮ ላይ መፅናትንና ከጥመት መራቅን አላህን መጠየቅ ነበር። አነስ ቢን ማሊክም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህን ዱዓ በማብዛታቸው ተደነቀ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልቦች ከአላህ ጣቶች መካከል በሁለቱ ጣቶች መሀል እንደሆኑና እንደፈለገም እንደሚያገለባብጣቸው ነገሩት። ቀልብ የኢማንና ክህደት መኖሪያ ናት። ቀልብ ቀልብ ተብሎ የተሰየመው በብዛት ስለሚገለባበጥ ነው። ቀልብ ድስት በሚንተከተክ ጊዜ ከሚገለባበጠው በላይ ይገለባበጣል። አላህ ለሻለት ሰው ቀልቡን በቀናው መንገድ ላይና በኢስላም ላይ ያፀናለታል። አላህ ጥመት የሻለትን ሰው ደግሞ ቀልቡን ከቀናው መንገድ ወደ ጥመት ያዞርበታል።