አላህ ኢስላምን ምንም ሳይጣመም በተዘረጋ ቀጥተኛ መንገድ መሰለው፤ በዚህ መንገድ ዳርና ዳር ሁለት ዙሪያውን የከበቡት አጥሮች አሉ እነሱም የአላህ ድንበሮች ናቸው፤ እነዚህ ሁለት አጥሮች የተከፈቱ በሮች ሲኖራቸው እነሱም የአላህ ክልከላዎች ናቸው፤ በመንገዱ የሚያልፍ ሰው በበሩ ውስጥ የሚገኘው ግልፅ እንዳይሆንለት በነዚህ በሮች ላይ የተዘጋጀ መጋረጃ አለ፤ በመንገዱ መነሻ ሰዎችን "መንገዳችሁን ወደጎንና ጎን ሳትዘነበሉ ቀጥ ብላችሁ ሂዱ!" እያለ የሚጠቁምና የሚመራ ተጣሪ አለ። ይህ ተጣሪም የአላህ መጽሐፍ ነው፤ እዚህ ቦታ ላይ የመንገዱ አናት ላይ ሆኖ የሚጣራ ሌላ ተጣሪም አለ፤ ይህ ተጣሪ መንገደኛው እነዛን የበሮቹ መጋረጃ ትንሽ ለመክፈት ባሰበ ቁጥር "ወዮልህ እንዳትከፍተው! መጋረጃውን ከከፈትከው ነፍስህን ውስጡ እንዳትገባ መቆጣጠር ስለማትችል ትገባለህ!" እያለ የሚያስጠነቅቀው ነው። ይህ ተጣሪም በሁሉም ሙስሊም ቀልብ ውስጥ የሚገኝ የአላህ መካሪ ነው። በማለት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምሳሌውን ፍቺ አብራሩት።