ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከፍ ያለው አላህ በሐዲሠል ቁድስ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ። "የፋቲሐን ምእራፍ በሶላት ውስጥ በኔና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፈልኩት። ግማሹ ለኔ ግማሹ ለርሱ ነው። የመጀመሪያው ክፍል: ለአላህ ምስጋና፣ ውዳሴና ልቅና ማቅረብ ሲሆን በዚህ ላይ ምርጥ ምንዳን እመነዳዋለሁ። ሁለተኛው ክፍል: መዋደቅ፣ ዱዓ ማድረግ ሲሆን እቀበለዋለሁም የጠየቀኝንም እሰጠዋለሁ። ሰጋጁ {الْحَمْدُ لِلهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ} (ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው፤ የዓለማት ጌታ ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህ "ባሪያዬ አመሰገነኝ!" ይላል። ሰጋጁ {الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ} (እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህም "ባሪያዬ በኔ ላይ አወደሰ፣ አሞገሰኝም፣ በፍጡሮቼ ላይ አጠቃላይ ፀጋዎችን መዋሌንም እውቅናን ሰጠ።" ይላል። ሰጋጁ {مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ} (የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህም "ባሪያዬ አላቀኝ!" ይላል። ይህም ትልቅ ክብር ነው። ሰጋጁ {إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ} (አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን።) ያለ ጊዜ አላህም: "ይህ በኔና በባሪያዬ መካከል ያለ ቃል ኪዳን ነው። ይላል። የዚህ አንቀፅ የመጀመሪያው ግማሽ ለአላህ ነው። እሱም (አንተን ብቻ እንግገዛለን።) የሚለው ነው። ይህም በአላህ ተመላኪነት እውቅና መስጠትና በዒባዳ ምላሽ መስጠት ነው። በዚህም በአንቀፁ ውስጥ ለአላህ የሆነው የመጀመሪያው ግማሽ ይጠናቀቃል። የአንቀፁ ሁለተኛው ግማሽ ደግሞ ለባሪያው ነው። እሱም (አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን።) የሚለው ነው። ይህም ከአላህ እገዛ መፈለግና አላህ ባሮቹን ለማገዝ የገባውን ቃልኪዳኑን መከጀል ነው። ሰጋጁ {اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ، صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلا الضَّالِّينَ} (ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፤ የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ።) ) ያለ ጊዜ አላህም "ይህ ከባሪያዬ የመጣ መዋደቅና ተማፅኖ ነው። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው። ልመናውን ተቀብዬዋለሁ።" ይላል።