መልአኩ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከሰማይ በር ሲከፈት እንደሚያሰማው አይነት ድምፅ ሰማ። ጂብሪልም ራሱንና አይኑን ወደ ሰማይ ቀና አደረገ። ቀጥሎ ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ይህ የሰማይ በር ዛሬ እንደተከፈተና ከዚህ ቀን በፊትም በፍፁም ተከፍቶ እንደማያውቅ ነገራቸው። ከሰማይም ወደ ምድር ከመልአኮች መካከል ከዛሬ በቀር ወርዶ የማያውቅ አንድ መልአክ ወረደ። መልአኩም ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አላቸው: ከአንተ በፊት ለማንም ነቢይ ባልተሰጡና ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለቱ ብርሃኖች አበስርሃለሁ። እነርሱም: የፋቲሓ ምዕራፍና የበቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎቹ ሁለት አንቀጾች ናቸው። አስከትሎም መልአኩ እንዲህ አለ: አንድም ሰው ከነርሱ አንድ ፊደል እንኳ ብትሆን ካነበበ አላህ በውስጧ ያለውን መልካም ነገር፣ ተማፅኖና ፍላጎት ይሰጠዋል።