ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መመሪያ መካከል ለመተኛት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ ልክ ዱዐ እንደሚያረግ ሰው መዳፋቸውን ሰብስበው ከፍ ያደርጉት ነበር። በሱም ላይ ከትንሽ ምራቅ ጋር በመቀላቀል ቀለል ያለ መንፋት በአፋቸው እየነፉበት ሶስት ምእራፎች ያነቡበታል። {ሱረቱል ኢኽላስ}ን፣ {ሰረቱል ፈለቅ}ን፣ {ሱረቱ አንናስ}ን ከዚያም የቻሉትን ያህል የሰውነታቸውን ክፍል ከጭንቅላታቸው፣ ከፊታቸውና ከሰውነታቸው የፊትለፊት ክፍል በመጀመር በመዳፋቸው ያብሱታል። ይህንንም ድርጊት ሦስት ጊዜ ይደጋግሙታል።