ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «አንድ ሰውዬ የሆነ ሰው {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን እየደጋገመ ሲያነብ ሰማ። የነጋም ጊዜ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመምጣት ነገሩን በሚያቃልል ሁኔታ ይህንን አወሳላቸው። የአላህም መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ (ቁል ሁወሏሁ አሐድ) የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: አንድ ሰውዬ ሌላ ሰው የ{ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን ምዕራፍ ሲያነብ ሰማ። ምሽቱን ሁሉ ሌላ ምዕራፍ ሳይጨምር እርሷን ብቻ ነበር እየደጋገመ የሚያነበው። የነጋም ጊዜ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመምጣት ይህንን አወሳላቸው። የጠያቂው አነጋገርም ምዕራፏን ያሳነሳት ይመስላል። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አፅንዖት ለመስጠት በመማል "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የኢኽላስ ምዕራፍ ትሩፋትን እንረዳለን። እርሷም የቁርአንን ሲሶ የምትስተካከል መሆኗ፤
  • የለይል ሶላት ሲሰገድ ጥቂት አንቀጾችን በመቅራትና እነርሱን በመደጋገም መስገድ እንደሚፈቀድ፤ ይህንንም አሳንሶ ማየት እንደማይገባ እንረዳለን።
  • ማዚሪይ እንዲህ ብለዋል: «በሐዲሡ ለማለት የተፈለገውን በማስመልከት "ቁርአን ሶስት ክፍሎች አሉት። እነርሱም: ታሪክ፣ ህግጋትና የአላህ ባህሪያት ናቸው። {ቁል ሁወሏሁ አሐድ} የአላህን ባህሪ ብቻ የምታወሳ ናት። ስለዚህ ከሶስቱ ክፍሎች አንዱ ክፍል ናት ማለት ነው።" ተብሏል። ይህቺን ምዕራፍ ማንበብ የሚያስገኘው ምንዳ ሲነባበር የቁርአን ሲሶ ሲነበብ ሳይነባበር የሚያስገኘውን ያህል ይሆናል ማለት ነውም ተብሏል።»