ኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ። ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኡበይ ቢን ከዕብን የአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቁ አንቀፅ ማን ናት? በማለት ጠየቁት። መልስ ለመስጠት ካመነታ በኋላ አየቱል ኩርሲይ ናት {አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} በማለት መለሰ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በዕውቀትና ጥበብ የተሞላ መሆኑን ለመጠቆም ደረቱን በመምታት በዚህ ዕውቀት እንዲደሰትና እንዲገራለት ዱዐ በማድረግ ትክክለኛ መልስ እንደመለሰ በመጥቀስ አበረታቱት።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- ትልቅ ደረጃ፤
  • አየቱል ኩርሲይ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቋ አንቀፅ በመሆኗ መሸምደዱ፣ ትርጉሙን ማስተንተኑና እርሱን መተግበር ተገቢ ነው።