explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ከሶላት አራቁቶ እንደመቃብር የማይሰገድበት ማድረግን ከለከሉ። በመቀጠልም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ ከሚቀራበት ቤት እንደሚሸሽ ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ቤት ውስጥ ሱና ሶላቶችን የመሰሉ አምልኮዎችን ማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ወደ ሺርክና በተቀባሪው ላይ ወሰን ወደ ማለፍ ከሚያዳርሱ መንገዶች አንዱ ስለሆነ ከጀናዛ ሶላት በስተቀር መቃብር ግቢ ውስጥ ሶላት መስገድ አይፈቀድም።
  • መቃብር ዘንድ መስገድ መከልከሉ ሶሐቦች ዘንድ የተረጋገጠ ጉዳይ ስለሆነ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቶችን ልክ እንደመቃብር የማይሰገድባቸው ከማደረግ ከለከሉ።