ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን አዘውትሮ በመቅራት ላይ አነሳሱ። ቁርአን የትንሳኤ ቀን ለሚያነቡትና በርሱ ለሚተገብሩ ሰዎች ያማልዳል። ቀጥለውም የበቀራንና የአሉ ዒምራንን ምዕራፎች በማንበብ ላይ ጠንከር አድርገው አነሳሱ። ስለሚመሩና ስለሚያበሩም አብሪዎች ብለው ሰየሟቸው። እነርሱን የማንበብ፣ ትርጉማቸውን የማስተንተንና ውስጣቸው ባለው የመተግበር ምንዳና አጅርም የትንሳኤ ቀን እንደ ሁለት ደመና ወይም ሌላ ጥላ ወይም እርስ በርስ ተጠባብቀው ክንፋቸውን እንደዘረጉ ሁለት የበራሪ መንጋ ተመስለው ባለቤቶቻቸውን አስጠልለው የሚከላከሉለት መሆናቸውን ተናገሩ። አስከትለውም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የበቀራን ምዕራፍ አዘውትሮ በመቅራት፣ ትርጉሙን በማስተንተንና ውስጡ ባለው በመስራት ላይ አጠንክረው አነሳሱ። ይህም ውስጡ በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ትልቅ በረከትና ጥቅም ስላለው እና ይህንን መተውም የትንሳኤ ቀን ቁጭትና ፀፀት ይዞ ስለሚመጣ ነው። ከዚህ ምዕራፍ ደረጃዎች መካከልም ደጋሚዎች ይህንን ምዕራፍ የሚቀራን ሰው ሊጎዱ አለመቻላቸው ተጠቃሽ ነው።