ሑዘይፋህ ቢን አል'የማን -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንዳስተላለፉት: «ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መተኛት የፈለጉ ጊዜ እጃቸውን ጭንቅላታቸው ስር ያኖሩ ነበር። ቀጥለውም እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ ቂኒ ዐዛበከ የውመ ተጅመዑ አው ተብዐሡ ዒባደክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ባሮችህን በምትሰበስብበት ወይም በምትቀሰቅስበት ቀን ከቅጣትህ ጠብቀኝ።" ማለት ነው። ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ ዘግበውታል።