ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳንድ የጠሀራ ህግጋትን ገለፁ። ከነርሱም ውስጥ: የመጀመሪያው: ዉዱእ ያደረገ ሰው ውሀን ወደ አፍንጫው ውስጥ ስቦ ማስገባትና ድጋሚ ከአፍንጫው ማስወጣት ይገባዋል። ሁለተኛው: ሽንት ቤት ውስጥ ከርሱ የሚወጣውን ቆሻሻ ከውሃ ውጪ በድንጋይና በመሳሰሉ ነገሮች ማንፃትና ማስወገድ የፈለገ ሰው የመፀዳጃው ብዛት በጎዶሎ ቁጥር መሆን እንደሚገባ፤ ቢያንስ ሶስት ሲሆን ከፍተኛው ከርሱ የሚወጣውን ቆሻሻ የሚቆርጥና ቦታውን የሚያፀዳለት ያህል ነው። ሶስተኛው: ከሌሊት እንቅልፍ የነቃ ሰው እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና ነጃሳ አለመንካቱን ስለማይተማመን እንዲሁም ለሰው ልጅ የሚጎዳ ወይም ውሃውን የሚያበላሽ ነገርን ሰይጣን ወደ እጁ ተሸክሞ አምጥቶ ተጫውቶበት ሊሆንም ስለሚችል እጁን እቃው ውስጥ ሳይነክር ሶስት ጊዜ ሳያጥብ ዉዱእ ለማድረግም መዳፉን እቃ ውስጥ መክተት አይገባውም።