ሰልማን አልፋሪሲይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: አጋርያኖች በኛ ላይ ለማሾፍ እንዲህ አሉን: ነቢያችሁ ከሽንት ወይም ከሰገራ እንዴት እንደምትፀዳዱ ሳይቀር ሁሉንም ያስተምራችኋል አይደል? ሰልማንም እንዲህ በማለት መለሰ: "አዎ የመፀዳዳትን ስነስርዓት አስተምረውናል። ከዚህም መካከል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተፀዳዳን በኋላ ቀኝ እጅን ከነጃሳ ለመጠበቅና ለቀኝ እጅ ክብር በቀኝ እጅ ኢስቲንጃእ ከማድረግ ወይም ሽንታችንንና ሰገራችንን በምንፀዳዳበት ወቅት ወደ ከዕባ ዞረን ከመፀዳዳት ከልክለውናል። በእንስሶች ፍግና አጥንት ከማደራረቅ ከልክለውናል። ዉዱእ ያጠፋና ተፀዳድቶ የሚያደራርቅ ሰውም ከሶስት ድንጋይ ባነሰ እንዳያደራርቅ ከልክለዋል።