ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ። "ሁለቱም አያፀዱም።" ብለዋል።» ሶሒሕ ነው። - ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።