ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን ሽምደዳውን አሳምሮ፤ አስተማማኝ በሆነ መልኩ፤ ውብና ቆንጆ አድርጎ የሚያነብ ሰው በመጪው ዓለም ያለው ምንዳ ደረጃው ታዛዥና የተከበሩ ከሆኑ መላእክቶች ጋር እንደሆነ፤ ቁርአንን የመሸምደድ አቅሙ ደካማ ስለሆነ ቁርአን ማንበብ በርሱ ላይ ከባድና አስቸጋሪ ሆኖበት እየተንተባተበና እየመላለሰ የሚያነብ ከመሆኑም ጋር ሳያቋርጥ ዘውትር የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ እንዳለው ተናገሩ። አንዱ ምንዳ የማንበቡ ምንዳ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የመላለሰበትና ተቸግሮ የማንበቡ ምንዳ ነው።