አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?" እኛም "አዎን" አልን። እሳቸውም "አንዳችሁ በሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸው ሶስት አንቀፆች ከሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎች ለሱ የተሻሉ ናቸው።" አሉ። ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰላት ውስጥ ሶስት አንቀፆችን በማንበብ የሚገኘው ምንዳ አንድ ሰው ቤቱ ውስጥ ሶስት የሰቡ ትላልቅ እርጉዝ ግመሎችን ከሚያገኝ እንደሚበልጥ ገለፁ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሰላት ውስጥ ቁርኣን የማንበብ ትሩፋት መገለፁ።
  • መልካም ሥራዎች ከጠፊዋ ዱንያ መጣቀሚያ የተሻሉና ዘውታሪዎች ናቸው።
  • ይህ ትሩፋት ሦስት አንቀፆችን በማንበብ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሰጋጁ ሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸውን አንቀፆች በጨመረ ቁጥር የሚያገኘው ምንዳ ለሱ በሚያነባቸው ቁጥር ልክ የእርጉዝ ግመሎች ከሚሰጠው የተሻለ ነው።