ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን እየነገሩን ነው፡- አጋርን ከመፈለግ ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃው አሏህ ነው። እርሱም ከምንም የተብቃቃ ራሱን የቻለ ነው። አንድ ሰው መልካም ነገርን ሲያደርግ ለአላህም ለሌሎችም ብሎ ቢያደርገው አላህ ይህንን ስራውን ይተውለታል፤ አይቀበለውም፤ ወደራሱ ይመልስለታል። ስለዚህም ጥራት የተገባው አሏህ ጥርት ባለ መልኩ ለርሱ ተብሎ የተሰራውን መልካም ስራ ካልሆነ በቀር ሌላን ስራ ስለማይቀበል ኢኽላስን ለርሱ ማድረግ ግዴታ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሽርክ መልካም ስራዎች ተቀባይነት እንዳያገኙ ግርዶ ስለሆነ በሁሉም መልኩ መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
  • ስራን ለአሏህ ጥርት አድርጎ ለመስራትስለሚያግዝ የአሏህን ሙሉ ተብቃቂነትና ታላቅነት ማስተዋል እንደሚያስፈልግ እንረዳለን።