የተወሰኑ ጭፍሮች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። ብዛታቸውም አስር ነበሩ። ከነርሱ መካከል ከዘጠኙ ጋር በኢስላም ላይና እርሳቸውን በመከተል ላይ ቃል ተጋቡና ከአስረኛው ጋር ቃልኪዳን ሳይጋቡ ቀሩ። የዚህን ምክንያት የተጠየቁ ጊዜም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: እርሱ ላይ ሒርዝ አለበት። (ሒርዝ) ማለት፦ ዓይንን ወይም ጉዳትን ለመከላከል ከጨሌና ከሌላም ነገር የሚሰራ የሚታሰር ወይም የሚንጠለጠል ነው። ሰውዬውም ወደ ሒርዙ ስፍራ እጁን ከቶ በመቁረጥ ከሒርዙ ጠራ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዚህ ጊዜ ቃልኪዳን ተጋቡት። ከሒርዝ ለማስጠንቀቅና ብይኗን ለመግለፅም እንዲህ አሉ: "ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል።"