explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ያመጡትን ሸሪዓዊ ወሰን ያለ ምንም መመሪያና እውቀት ወሰን ተላልፈው በንግግራቸውም ይሁን በተግባራቸው በእምነታቸውም ይሁን በአለማዊ ጉዳያቸው ፅንፍ የሚረግጡ ሰዎች ያለባቸውን ውርደትና ኪሳራ ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በየትኛውም ጉዳይ በተለይም በዒባዳና ፃድቃንን በማላቅ ረገድ ወሰን ማለፍና ያላቅም መንጠራራት መከልከሉንና ከእንዲህ አይነቱ ነገር መራቁ በየትኛውም ጉዳይ ላይ እንደሚበረታታ እንረዳለን።
  • በአምልኮም ይሁን በሌላው ጉዳይ ተስተካክሎ የተሟላውን መፈለግ እንደሚገባና ይህም የሚሆነው ሸሪዓውን በመከተል መሆኑን እንረዳለን።
  • አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ጠንከር ማድረግ እንደሚገባ፤ ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንኑ እንኳ ሲናገሩ ሶስት ጊዜ ደጋግመው ነውና የተናገሩት።
  • የእስልምና ገራገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን።