ከአቢል ሀያጅ አልአሰዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ለኔ እንዲህ አለኝ: 'የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው።'" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።