ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ጉዞ ላይ ሰዎች በሚያድሩበት የግመልና የመኝታ ድንኳናቸው ስፍራቸው ውስጥ ባሉበት ወደ ሰዎች በግመል ላይ የምትንጠለጠል ገመድ እንድትቆረጥ የሚያዝ አንድን ሰው ላኩ። ይህም የቀስት ገመድም (ወተር) ይሁን ወይም ከርሱ ውጪ የቃጭልና የጫማ ገመድ የመሳሰሉም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። ይህም የሰው አይን ፈርተው ያስሩት ስለነበር ነው። እንዲቆርጡት የታዘዙበት ምክንያትም ከነርሱ ላይ አንዳችም ነገር ስለማይመልስ ነው። ጥቅምና ጉዳት አጋር በሌለው በአላህ እጅ ብቻ ነውና።