የአማኞች እናት ኡሙ ሰለማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - በሐበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስእሎች፣ ጌጦችና ቅርፆች ማየቷን በመደነቅ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የነዚህን ስእሎች መደረግ ምክንያት ገለፁ። "እነዚህ አሁን አንቺ የምታወሺያቸው በመካከላቸው ደግ ሰው የሞተ ጊዜ በቀብሩ ላይ መስጂድ ይገነቡና በውስጡ ይሰግዱበታልም እነዚህንም ስእሎች ይስላሉ።" አሉ። ይህንን የሚፈጽም ሰው አላህ ዘንድ ክፉ ፍጡር እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ድርጊቱ በአላህ ወደ ማጋራት ስለሚያዳርስ ነው።