ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።" ሶሒሕ ነው። - رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከትንሳኤ ቀን መቅረብና የዱንያ መጠናቀቅ ምልክቶች መካከል አንዱ ሰዎች መስጂዶችን በማስዋብ መፎካከራቸው ነው። ወይም አላህን ከማውሳት ውጪ ለሌላ አላማ ባልተገነቡ መስጂዶች ውስጥም በዱንያቸው መፎካከራቸው ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በመስጂዶች መፎካከር ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ለአላህ ተብሎም ስላልተሰራ ተቀባይነት የሌለው ስራ ነው።
  • በቀለም፣ በቅርፃ ቅርፅና በጽሑፎች መስጂዶችን ማስጌጥ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ሰጋጆችን ሲመለከቱት ስለሚያዘናጋቸው ነው።
  • ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "የዚህን ሐዲሥ እውነተኝነት ዛሬ ላይ መታየቱ ምስክር ይሆንልናል። እርሱም ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አስደናቂ ተአምራቶች መካከል አንዱ ነው።"