ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።