ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በአባት መማልን እንደሚከለክል ተናገሩ። ስለዚህም መማል የፈለገ ሰው በአላህ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማል። ቀጥለውም ዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ሲከለክሉ ከሰሙ ጀምሮ ሆን ብለውም ይሁን ሌላ ሰው ከአላህ ውጪ መማሉን በመናገር መልኩም ይሁን ምለው እንደማያውቁ አወሱ።