ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከተወሰኑ ሶሐቦች የሆኑ ጉዳዮችን አጥብቆ ለመያዝ ቃልኪዳን እንዲጋቡዋቸው ሶስት ጊዜ ፈለጉ። የመጀመሪያው: አላህን ትእዛዙን በመተግበር ክልከላውን በመራቅ በብቸኝነት ማምለክና በርሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው። ሁለተኛው: አምስቱን ግዴታ ሶላቶች በቀንና በምሽት ቀጥ አድርጎ መስገድ ነው። ሶስተኛው: የሙስሊሞችን ጉዳይ እንዲመራ ለተሾመ ሰው በመልካም ጉዳዮች ሰምቶ መታዘዝ ነው። አራተኛው: ሁሉንም ጉዳያቸውን ወደ አላህ በማስጠጋት ሰዎችን አንዳችም ነገር አለመጠየቅ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ሲናገሩ ድምፃቸውን ዝግ አደረጉ። ሐዲሡን ያስተላለፈው፦ "ከነዚህ ሶሐቦች የተወሰኑትን የአንዳቸው አለንጋ ሲወድቅ እንኳ ወርዶ በራሱ ያነሳዋል እንጂ አንድም ሰው አለንጋውን እንዲያቀብለው የማይጠይቅ ሆነው ተመልክቻቸዋለሁ።" ብሎ እስኪገልፃቸው ድረስ ሶሐቦቹ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የተጋቡትን ቃልኪዳን ተግባራዊ አድርገውታል።