ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አጋርያኖች ከአላህ ውጪ ያመልኳቸው በነበሩትና ለክህደታቸውና ጥመታቸው ምክንያት በነበሩት ጣዖታት ከመማል ከለከሉ። በድንቁርና ዘመን የዐረቦች ልማድ ከነበሩት ነገሮች መካከል ለመኩራራትና ለማላቅ በአባቶቻቸው መማል ነበርና ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአባቶች ከመማልም ከለከሉ።