ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛውንም ሙስሊም በንግግሩ "አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)" ከማለት ከለከሉ። ወይም "አላህና እከሌ ሽተውት (ፈልገውት)" ከማለት ከለከሉ። ይህም የሆነው የአላህ መሻትና ፍላጎት ልቅ በመሆኑ አንድም የሚጋራው ስለሌለ ነው። "እና" የምትለውን ቃል በአጣማሪነት መጠቀማችን በመሻት በኩል ከአላህ ጋር የሚጋራ ሌላ አካል እንዳለና በመካከላቸው ያለው መሻትም እኩል እንደሆነ ይጠቁማል። ነገር ግን "አላህ ሽቶት ከዚያም እከሌ ሽቶታል።" ይበል። "ከዚያም" የሚለውን ቃል "እና" በሚለው ተለዋጭ አድርጎ በመጠቀም የባሪያን መሻት የአላህን መሻት ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን ግልፅ ያድርግ። ምክንያቱም "ከዚያም" የምትለው ቃል ቅደም ተከተልን ትጠቁማለችና።