የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠንቶባቸው በርሱ ምክንያት የሞቱበት በሆነው በሽታቸው ወቅት እንዲህ ይሉ እንደነበር ተናገረች: "አይሁዶችና ክርስቲያኖችን አላህ ይርገማቸው። ከእዝነቱ ያባራቸው። ይህም እነርሱ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስጂድ አድርገው ስለያዙ ነው።" ይህም መቃብሩ ላይ መስጂድ በመገንባት ወይም እርሱ ዘንድ ወይም ወደርሱ ዞሮ በመስገድ ነው። ቀጥላም ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - "ይህ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ክልከላና ማስጠንቀቂያ ባይኖር ኖሮና እንዲሁም አይሁዶችና ክርስቲያኖች በነቢያቶቻቸው መቃብር ላይ እንደፈፀሙት በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀብር ላይም እንዳይፈፀም ሶሐቦች ባይፈሩ ኖሮ ቀብራቸው ይፋና ግልፅ ይሆን ነበር።" አለች።