በምላሱ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ያለና የመሰከረ ሰው ፤ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደና ከኢስላም ውጪ ካሉ ሁሉ እምነቶች የጠራ ሰው በሙስሊሞች ላይ ገንዘቡና ደሙ እርም ይሆናል። እኛ ውጫዊ ከሆኑ ስራዎቹ በስተቀር መፈላፈል አይፈቀድልንም። በኢስላማዊ ህግጋት ይህንን የሚያስገድድ አስገዳጅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ገንዘቡም እንደማይነጠቅ ደሙም እንደማይፈስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። የትንሳኤ ቀን ሂሳቡን በበላይነት የሚመራው አሏህ ነው። እውነቱን ከሆነ ይመነዳዋል። ሙናፊቅ ከሆነ ደግሞ ይቀጣዋል።