ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሽታ ከአንዱ ወደ ሌላው ያለ አላህ ውሳኔ በራሱ ይተላለፋል የሚለው የድንቁርና ዘመን ሰዎች ያምኑት የነበረው እምነት የተሳሳተ ከንቱ እምነት መሆኑን ተናገሩ። የገድ እምነትም ከንቱ አጉል እምነት ነው። እርሱም በማንኛውም የሚሰማ ወይም የሚታይ ወፍ ወይም እንስሳ ወይም አካል ጉዳተኞችን ወይም ቁጥሮች ወይም ቀናት ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች ላይ ተመርኩዞ ገደቢስነትን ማመን ነው። ወፍን ያወሱት በድንቁርና ዘመን የታወቀው ገድ ማለት በርሱ ስለነበር ነው። መሰረቱም ስራ ወይም ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ጉዳይ ሊጀምሩ ሲፈልጉ ወፍን ይለቃል። ወፊቱ ወደ ቀኝ ከበረረች ጥሩ ገድ በማመን ወደፈለገው ይጓዛል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረች ደግሞ ገደቢስነትን በማመን ከፈለገው ጉዳይ ይቆጠባል። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "አልፈእል" (በጎ ምኞት) እንደሚያስደስታቸው ተናገሩ። እርሱም የሰው ልጅ ከሰማው መልካም ቃል አንፃር የሚያጋጥመው የደስታና ሀሴት ስሜት ነው። ይህም በጌታው ላይ መልካም እሳቤ እንዲኖረው ያደርጋልና።