ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ያለን አካል መጣራትና ከአላህ ውጪ ካለ አካል እርዳታ መፈለግን የመሰለ ለአላህ ሊደረግ ግዴታ የሆነን አንዳች ነገር ለሌላ እየሰጠ የሞተ ሰው የእሳት ባለቤት መሆኑን ነገሩን። ኢብኑ መስዑድም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በአላህ ላይ አንዳችን ሳያጋራ የሞተ ሰው መመለሻው ወደ ጀነት ነው የሚለውን ጨመሩ።